ገንዘብ መስራት ~ ሕይወትን መኖር

ስለ ስር-ዓይን

ስር-ዓይን ለምን ተመሰረተ____? ስር-ዓይን የተመሰረተው በሰው ልጆች (ግለሰቦች/ ቤተሰብ) የኑሮ ዘይቤ የእለት ከእለት ፈተናዎች እና የንግድና አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን ፈተና ለመፍታትና ድልድይ ሆኖ የተሻለ የግለሰቦች የኑሮ ዘይቤ እና የንግድ ልውውጥ እንዲኖር ለማመቻቸት ነው።

.........
አላማችን ግላሰቦችን፣ የንግድና አገልግሎት አቅራቢ ድርጅቶችን እለታዊ ክወና ላይ አሸናፊ እንዲሆኑ አቅማቸውን ከፍ ማድረግ ነው። 
 

ተልዕኮ ~ ራዕይ ~ አላማ

ተልዕኮ

> የግለሰቦችንና የንገድ ድርጅቶችን እለታዊ ክንዋኔ ማቅለል፣ በየትኛውም የተሰማሩበት ዘርፍ ክንዋኔያቸውን ቀላል አድርገንላቸው በውጤቱ እንዲረኩ እና ስኬትን እንዲጎናፀፉ ማድረግ።    

ራዕይ

> የግለሰቦችን የኑሮ ዘይቤ እና የንግድ ድርጅቶችን እለታዊ ክንውን የሚያቀልና ይበልጥ ምርታማ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን የመፍትሄ አገልግሎት በማቅርብ በአለም አቀፍ ደረጃ መሪ ድርጅት መሆን።         

አላማ

> ለደንበኞቻችን የተረጋጋ ሕይወት እንዲኖራቸው ማስቻል፣ ለግል ሕይወታቸው እና በሞያቸው ለሚያገለግሉበት የሚያስፈልጋቸዉን ቁስና እርዳታ ማግኘት እንዲችሉ ማረጋገጥ።

> ከግለሰብ ተጠቃሚዎች እስከ ትላልቅ ድርጅቶች ሁሉንም የመድረኩ ተዋንያኖችን እኩል ተጠቃሚ በማድረግ፣ አቃፊና ተመጋጋቢ የገበያ ስርዓት ውስጥ የተረጋጋ ገበያ በአለም አቀፍ ደረጃ መፍጠር። 

> በአለም አቀፍ ደረጃ ኢኮኖሚውን በማንቀሳቀስ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የስራ እድሎችን መፍጠር እና አዲስ፣ ቀላል ከኑሮ ዘይቤ ጋር የሚጣጣም የስራ ልማድ መፍጠር።

 ማንን ነው የምናገለግለው?

> ለማገልገል የተዘጋጀነው እና የምንሰራው ከተለያዩ የንግድና አገልገሎት ሰጪ ድርጅቶች፣ እንዲሁም አገልግሎታቸንን ለመጠቀም ወደ ድህረ ገፃችን የሚመጡትን ማንኛውም የሀገር አቀፍና አለም አቀፍ የድህረ ገፅ ንግድ ህጉ ሚፈቅድላቸውን፡- 

ጊዜ የሚያጥራቸውን ባለሞያዎች፣ ኢንተርፕረነሮች፣ ቤተሰቦች፣ ተማሪዎች እና ትላልቅ ድርጅቶች ደንበኞችን ቢሆንም፣  በመሰረታዊነት ይህንን የመገልገያ መድረክ በዋናነት 4 (አራት) ተገልጋይ ቤተሰቦቻችንን አማካኝ አድርገን ነው ያዘጋጀነው። እነሱም፡ -

#ሻጮች #ገዢዎች #ስራ ፈላጊዎች/ባለሞያዎች እና #ኢንተርፕረነሮች/ኢንቨስተሮች ናቸው። 

> ለማገልገል ያዘጋጀናቸው መፍትሄዎቻችን፣ ለእያንዳንዱ ደንበኛችን (ችግራቸውን መፍታት ለሚፈልጉ)፣ እለታዊ ክንዋኔያቸውን እና የረጅም ጊዜ ግባቸውን በብልሃት ለማሳካት እንዲያስችላቸው የተመጠኑ ናቸው።

የምናቀርባቸው አገልግሎቶች

በስር-ዓይን የምንሰጣቸው አገልግሎቶች ግለሰቦችም እለት ከእለት ህይወት ውስጥ የሚጋፈጧቸውን እና በንግዱ አለምም የተለመዱ መሰረታዊ ችግሮችን በተመጣጣኝ መፍትሄ የሚፈቱ በልካቸው የተዘጋጁ ናቸው።

 

ለሻጮች

(ለግለሰቦች) እና (ለድርጅቶች) ከቅድሚያ ማማከር ጀምሮ፣ የሚሸጡትን ማስመረጥ፣ ከአቅራቢ ማገናኘት፣ ከተረጋገጠ እና ወቅታዊ ደንበኛ ጋር ማገናኘት፣ የክፍያ ጉዳዮችንና ብድር ማመቻቸት ወይም ከሸጡ በኋላ ለምርት/ አገልግሎት አቅራቢ ለመክፈል ማመቻቸት፣ አመራች ከሆኑ ከጥሬ እቃ አቅራቢዎች ማገናኘት፣ የመጋዘን አገልግሎት መስጠት፣ ከደንበኞቻቸው የክፍያ መቀበያ መንገድ ማመቻቸት፣ የማጓጓዝና ለደንበኞች የማድረስ ስራን በኃላፊነት መስራት እና ሌሎችም እዚህ ያልተጠቀሱ ዘርፈ ሰፊ አገልግሎቶች።

> ለመሸጣቸው እርግጠኛ ናቸው።

> ወጪያቸው ያነሰ ነው።

> ገቢያቸው የተረጋገጠ እና ትክክለኛውን ምርት ለትክክለኛው ደንበኛ ብቻ ለማቅረብ ይሰራሉ።

 

ለገዢዎች

የተለያዩ አመታዊ ወጪያቸውን እስከ በ80% የሚቀንሱ እና የኑሮ ዛይቤያቸውን የሚያዘምኑ እንደ (አስቤዛ፣ የቤት ኪራይ ክፍያ፣ የእዳ ክፍያ፣ የት/ት ክፍያ፣ የጤና ወጪ ክፍያ እና ሌሎችም እለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ፣ አመታዊ ወጪዎቻቸውን/ ክፍያዎቻቸውን) እና የመሳሰሉ ጥቅል አገልግሎቶች እና እንዲሁም፣ ሻጭ ሆነው ወይም በቀላሉ ስራ ተቀጥረው ወይም ኢንተርፕረነር/ ኢንቨእስተር ሆነው ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ ማድረግ። 

> በአነስተኛ ወጪ እውነተኛ ጥቅም ያላቸውን ምርትና አገልግሎቶች ያገኛሉ።

> የሚያስፈልጋቸዉን ብቻ በሚያስፈልጋቸው ወቅት በራቸው ላይ ያገኛሉ።

> ከጤናቸው ጋር የሚስማማውን ብቻ ይመርጣሉ።

 

ለስራ ፈላጊዎች

በ1 ደቂቃ የሚሆናቸውን የተረጋገጠ ስራ እናገናኛቸዋለን። ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ቪዛ/ መኖሪያ ፍቃድ (ከሀገር ውጪ)፣ ኢንሹራንስ፣ መኖሪያ፣ ምግብ፣ መጓጓዣ፣ ስፖርት መስሪያ፣ መዋኛ እና ሌሎችም አስፈላጊ ቁሶችና አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እና ለሌሎች የተረጋጋ ሕይወት በጋራ ለመስራት እንዲችሉ እናመቻቻለን። 

አቅማቸውን ይበልጥ ለመገንባት ጎንለጎን ንግድ/ ቢዝነስ እናስጀምራቸዋለን። ቤት፣ መኪና፣ ት/ት፣ ብድር እና ሌሎችም የሚፈልጓዋቸውን ምርትና አገልግሎቶች የሚያገኙበት የተለያዩ ጥቅል አገልግሎቶች ተዘጋጅቶላቸዋል። 

> ስራ ከተረጋጋ ሕይወትጋር ያጋኛሉ።

> ስራን ከገንዘብ በላይ ለጥልቅ ስሜታቸው ነው የሚሰሩት።

> ከስራ መባረር የለም። እናስተምራቸዋለን፣ አብረን እናድጋለን።

 

ለኢንተርፕረነሮች/ ኢንቨስተሮች

አዳዲስ ትርፋማነታቸው የተረጋገጠ እና በኢንሹራንስ የተደገፉ የሀብት ማፍሪያ ሃሳቦችን ከመስጠት እስከ የነፃ እጅ አገልግሎት መስጠት፣ ፈሰስ ያደረጉበትን ንግድ ወይም አገልግሎት በሙሉ ኃላፊነት እስከ ማስተዳደር፣ በእዳ ያፈሩትን ሀብት እንዳያጡት መፍትሄ በልክ መጥነን ጥቅሎችን አዘጋጅተናል። 

> አዲስ እና ትርፋቸው የተረጋገጠ የኢንቨስትመንት ሃሳቦች ያገኛሉ። 

> ለማስተዳደር ብዙ ኪሎሜትር መሄድ ሳየጠበቅባቸው ሀብት ማፍራት ይችላሉ።

> ሕይወትን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ማጣጣም ላይና ለተፈጠሩለት አላማ ጊዜ ያገኛሉ።

እንዲሁም በነፃ እጅ አገልግሎታችን ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ጨምሮ ሌሎችንም የግላቸውንና የንግዳቸውን ያለፈ ችግር (እዳ...)፣ አሁን ያለ ፍላጎት (ወጪዎች፣ ብድር፣ ግዢዎች...) የወደፊት ግብ/ህልም/ ራዕይ (ቤት፣ መኪና፣ ድርጅት...) እና የመሳሰሉ ችግሮቻቸውን እንቀርፋለን፣ መፍትሄ በልክ እንመጥናለን፣ የሚፈልጉበት እንዲደርሱና የተረጋጋ ህይወት እንዲኖሩ እንሰራለን። 

በተጨማሪም፡- ከላይ የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች እና ጥቅሞች ይጋራሉ።

 

ዋና ዋና አገልግሎቶች

> ስራ መፍጠር/ ማመቻቸት፡

የተረጋገጠ ስራ ማገናኘት እና የቅጥር ሙሉ አገልግሎት!

> የንግድ ክንውን:

ከመነሻ እስከ መድረሻ፣ ከቢዝነስ ምስረታ እስከ እለታዊ የቢዝነስ ማስተዳድር ሙሉ የንግድ ስራ ክንውን!

> የፋይናንስ ክንውን መፍትሄ:

ችግር ፈቺ እና ዘመናዊ የኢንቨስትመንት፣ የክፍያዎች አና የእዳ ማፅዳት መፍትሄዎች! 

> የድህረ ገፅ ገበያ:

ማህበረሰብ አቀፍ የተረጋገጠ ደንበኛ ማግኛ አለም አቀፍ መግዣና መሻሻጫ ፕላትፎርም!  

ችግርዎን ተረድተናል

ነገሮች በጣም በፍጥነት በሚቀያየሩበት በዛሬው የአለማችን ሁኔታ የሚፈልጉትን ለማሳካት እንደተቸገሩ ተረድተናል።  
 
ትክክለኛውን ስራ ማግኘት ተቸግረዉ ሊሆን ይችላል፣ ንግድዎን ማስተዳደር እና ክንውኑን መቆጣጠር ተቸግርው ሊሆን ይችላል፣ ከገንዘብ ጋር የተገናኙ ችግሮች መፍቻቸው ርቆቦት ሊሆን ይችላል ወይንም ለከፈሉት ክፍያ ተመጣጣኝ ምርትና አገልግሎት የሚያገኙበት የተረጋጋ ታማኝ ገበያ ማግኘት ተቸግረው ይሆናል።  

እነኚህ እና መሰል ፈተናዎች፣ ለግል እና ለንግድዎ እድገት ከአቅም በላይ የሆኑ እንቅፋቶችን ከፊትዎ ሊደቅኑ ይችላሉ።

መፍትሄዎቻችን

እንደ ግል ሆነ እንደ ንግድ ድርጅት የገጠመዎትን ፈተና ስር-ዓይን ለእያንዳንዱ ተመጣጣኝ መፍትሄ አቅርቧል፡ -

> ከሀ-ፐ የተመቻቸ ሂደት፡

በድህረ ገፃችን አገልግሎቶቻችን ለእርስዎ ቀለው ተዘጋጅተዋል። ከእለታዊ ክንውንዎ እስከ የረጅም ጊዜ ግብዎ ፕሮጀክቶች።

ከስራ ፍለጋ እስከ ንግድዎን በኃላፊነት እስከ ማስተዳደር። ወጪዎን ቀንሰን፣ ገቢዎትን ከፍ አድርገን አቅምዎን ገንብተን፣ የተረጋጋ ሕይወት መኖር እንዲችሉ እስከ ማመቻቸት።

> ገንዘባዊ ጉዳዮችን ማቅለል፡

ብዙ ሳይደክሙ፣ ረጅም ጊዜ ሳይፈጅብዎት ገንዘባዊ/ ፋይናንሳዊ ችግሮችዎን የሚፈቱና ኢኮኖሚያዊ ኃላፊነትዎን የሚያቀሉ የመፍትሄ አገልግሎቶች አቅርበናል።

> አለም አቀፍ ገበያ፡

በሰፊው አውታረ መረባችን የእርስዎን የመግዛትና የመሸጥ ምቾት ለማረጋገጥ እና የግል እና የንግድዎን ፍላጎት ለመሙላት የአለም አቀፍ ገበያ መዳረሻ በር ቁልፍ አዘጋጅተናል። 

>  እርስ በእርስ የሚደጋገፍ ማህበረሰብ፡

ስር-ዓይንን ሲቀላልቀሉ፣ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን የሚያገኙት፣ ከዛም በላይ የሆነ አንዱ ለአንዱ እድገት እና ለጋራ ስኬት አብሮ ለመስራት ቆርጦ የተነሳን ማህበረሰብ ጭምር ነው የሚቀላቀሉት። እንኳን ደህና መጡ!

የመስራች መልዕክት

ውድ ስር-ዓይናዊያን

የተረጋጋ  ሕይወት ለእርስዎ ሁሌም! 

አብዛኛው ሰው በዛሬው ነገሮች በፍጥነት በሚቀያየሩበት አለም አብዘሃኛውን የሕይወት ክፍሉን እየኖረ አይደለም።

ይህም የሆነው ሰዎች ወጪያቸውን ለመሸፈንና የቅርባቸውን ለመደገፍ ገንዘብ ለማግኘት ብዙ መድከምና ረጅም ጊዜያቸውን ለመስጠት መገደዳቸው አንዱ ምክንያት ነው።

የምመኝላቹ 

በቀን ከ5-6 ሰዓታት፣ በሳምንት ከ3-4 ቀናት ብቻ እየሰራቹ፣ በተጨማሪም፣ - ጎን ለጎን የህልማቹን ቢዝነስ/ ንግድ ድርጅት መስርታቹ፣ ቀሪውን ጊዜ ለተፈጠራችሁት አላማ መኖሪያ እና የምትወዱትን ጠቃሚ እውቀት እየተማራቹበት፣ ባለ ትዳሮች ለቤተሰብ በቂ ጊዜ መስጠት እንድትችሉ፣ ባለ ድርጅቶች ህልማችሁን እንድትኖሩበት፣ በጠቅላላው ሁሉም የሚገባውን የተረጋጋ ሕይወት እንዲኖር እመኛለሁ!

ቃል እገባለሁ "ኢን-ሻ አላህ"

እዳ ያለባቹ እዳችሁን በቀላሉ የምትከፍሉበት፣ አንተርፕረነሮች ለቢዝነስ መጀመሪያ ብድር በቀላሉ የምታገኙበት፣ ንግድ ከፍታቹ ገበያ ያጣቹ በቃላሉ ደንበኛ ምታገኙበት፣ መግዛት የፈልጋቹ ትክክለኛ ምርት እና ተመጣጣኝ ክፍያ የምታገኙበት፣ ስራ ፈላጊዎች ስራ በ1 ደቂቃ የምታገኙበት፣ ኢንቨስተሮች የተረጋገጠ ትርፍ የምታገኙበት፣ እርስ በራሳችን የምንጠቃቀምበት ስራ፣ ንግድ፣ ተመጋጋቢ ፕላትፎርም እና የሕይወት ዘይቤ ምቹ ከቢዝነስ ያለፈ አለም ይሆናል።

ከእናንተ ጋር

አብረን እንደ አንድ አካል ቆመን ተመሳሳይ የሆነውን ተደጋጋሚ ፈተናዎች የበዙበትን ሕይወት፣ ወደ ተረጋጋ ሕይወት እንቀይራለን፣ እንኖራታለን።

ኑ ገንዘብን እንስራ ~ ሕይወትን እንኑራት

እያንዳንዱን የሕይወት ክፍላችንን መኖር እስክንችል፣ ሚፈታውን ለመፍታት፣ ሚስተካከለውን ለማስተካከል፣ ሚጨመረውን ለመጨመር ሜዳውንም ፈረሱንም ይዤ ተገኝቻለሁ።

"ገንዘብ መስራት ~ ሕይወትን መኖር"

 

አብዱረዛቅ አህመድ

መስራች (ስር- ዓይን)

CEO and Founder of Ser-Ayin

ዛሬውኑ ይቀላቀሉን!



ስር-ዓይንን ይቀላቀሉ፣ የሕይወት ፈተናዎትን የሚያስተናግዱበትን መንገድ ይቀይሩ፣ ካቀረብንልዎ የበዙ እድሎች የድርሻዎን ይቋደሱ፣ አዲስ የስኬት፣ እርጋታ እና እርካታ የተሞላበትን የሕይወት መዕራፍ ይጀምሩ! 

የእውነት የእርስዎን ሕይወት ተረጋግተው መኖር እንዲችሉ ለማመቻቸት እና ለመርዳት የተዘጋጀን ፕላትፎርም አጊኝተዋል!

እንኳን ደስ ያለዎ!

ጥ&መ

ስር-ዓይን ማለት ምን ማለት ?

የስር-ዓይን አጭር ትርጉሙ፡ - (ልቦና) (እራስን ወደ ውስጥ ማየ/ መመልከቻ)

- ስር (ስር)፣ (ውስጥ) (ወደ ውስጥ)

- ዓይን (ልቦና)፣ (ማያ)፣ (መመልከቻ)

የስያሜ መነሻ ሃሳብ፡ -

አሁን እንደ ግለሰብ፣ እንደ ማህበረሰብ የገጠሙን የበዙ ፈተናዎች፣ ሊገጥሙን ከቻሉበት አንዱ ምክንያት፣ ወደ ውጭ ማየት በሚችለው ዓይናችን ብቻ የሌሎችን ህይወት እያየን እንደነሱ ለምኖር እየሞከርን እና እራሳችንን እያጣን ስለሆነ ነው።

እራሳችን ውስጥ ያለውን የተሰጠንን ፀጋ በውስጠኛው ማያችን (በልቦናችን) ወደራሳችን ወደ ውስጥ መመልከት ብንችል.... የእኛን ምርጡን ማንነት ማየት፣ ማዘጋጀት፣ ማውጣት፣ መጠቀም እንጀምር እና ለራሳችንም ለሌሎችም ብርሃን መሆን እንችል ነበር።

(አብዱረዛቅ አህመድ)

(መስራች) (ስር-ዓይን)

የት ነው የምትገኙት?

አብዘሃኛዎቹ አገልግሎቶቻችን በድህረ ገፅ የሚሰጡ ናቸው።

እርስዎ የሚፈልጉት አገልግሎት ቀጥታ እኛ የምንሰጠው አገልግሎት ከሆነ በቢሮዋችን/ በአገልግሎት መስጫ መዓከላችን ለመገኘት ካስፈለገ፣ በዱባይ፣ በራስ አል-ኼማ እና በአዲስ አበባ በሚገኙ ቢሮዎቻችን ቀርበው ለመገልገል ቀድመው ባሉን የመገናኛ አማራጮች ቀጠሮ ያስይዙ።

እርስዎን ለማገልገል በጉጉት እንጠብቅዎታለን!

የጠየቁት የአገልግሎት አይነት በእኛ በኩል የቀረበ ነገር ግን በአጋር ድርጅቶቻችን/በሶስተኛ አካል የሚሰጡ አገልግሎቶች ከሆኑም በመገኛ አድራሻቸው እንዲያስተናግድዎ እናመቻቻለን። 

ህጋዊ ናቹ?

አዎ በሚገባ። ለምንሰጣቸው አገልገሎቶች አስፈላጊውን የንግድ ፈቃድ አሟልተናል። 

ለኢኮሜርስ አገልግሎታችን፡

ኢትዮጲያ፣ ከአዲስ አበባ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

የግብር ከፋይ መለያ ቁ፡ 0083702105

በንግድ ምዝገባ ቁ፡ AA/ADISM/2/0002327/2015

(1) በንግድ ስራ ፈቃድ ቁጥር፡ NL/AA/14/666/4388513/2015

የንግድ መጠሪያ ስም፡ ስር ዓይን ንግድ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር

የንግድ ስራ መስክ፡ (85125) የኤሌክትሮኒክስ ንግድ ፕላትፎርም አንቀሳቃሽ

 

በተጨማሪም፡ ለዴሊቨሪ አገልግሎታችን

(2)  በንግድ ስራ ፈቃድ ቁጥር፡ MT/AA/14/666/4389975/2015

የንግድ ስራ መስክ፡ (73111) የፖስታ እና ፈጣን የመልእክት መጓጓዣ ተግባራት

በዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ፣ ከራኬዝ 

(1) Ecommerce Services

LICENCE NO: 45004536

OPERATING NAME: Ser Ayin Services FZ-LLC  

ACTIVITY: Products and Services E-Trading

 

(2) General Trading

LICENCE NO: 7007752 

OPERATING NAME: Ser Ayin Services FZ-LLC  

 ACTIVITY: General Trading

This website uses cookies!